ዛሬ ማርች 8 ነው
Wingate News
New Events in GWPTC
Posted by admin on 2024-03-24 00:43:45 |
Last Updated by admin on 2024-03-24 02:03:28
Share: Facebook |
Twitter |
Whatsapp |
Linkedin Visits: 77
አርብ፡- የካቲት 29 ቀን 2016 ዓ.ም
ዛሬ ማርች 8 የሴቶች ቀን በኢትዮጵያ ለ48ኛ በዓለም አቀፍ ደረጃ ደግሞ ለ113 ጊዜ የሚከበር ሲሆን ማርች /መጋቢት/ 8 እንደ ጎርጎሮሳዊያን የዘመን ቀመር 1908 ላይ ኗሪነታቸው በአሜሪካ ኒውዮርክ ከተማ የሆኑና በተለይ ደግሞ በጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካዎች ሰራተኞች የነበሩ 15,000 ሴቶች በአደባባይ ወጥተው የሥራ ሰዓት እንዲሻሻል /እንዲያጥር/፣ የደመወዝ ክፍያ እኩልነት እንዲፈጠር እና የመምረጥ መብታቸው እንዲከበር ለጥያቄ የወጡበት ታሪካዊ ቀን ነው፡፡ ከዚያም ከአንድ ዓመት በኋላ የአሜሪካ ሶሻሊስት ፓርቱ የመጀመሪያውን ብሔራዊ የሴቶች ቀን አወጀ። በ1975 ዓ.ም ደግሞ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሴቶች ቀንን ለመጀመሪያ ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ በይፋ እንዲከበር ውሳኔ አስተላልፏል፡፡
ኮሌጃችንም የሴቶችን ቀን ምክኒያት በማድረግ ሰሞኑን በርካታ ማህበራዊ አገልግሎቶችን በትጋት እየተውጣ ይገኛል፡፡ ካከናውናቸው ተጓዳኝ ተግባራት መካከል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሴቶች፣ ህፃናት እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ በአቃቂ ቀሊቲ ላስገነባው የሴቶች ተሀዲሶና ክህሎት ማሰልጠኛ ማዕከል ለቤተ መጽሕፍት አገልግሎት 116 ሸልፎች፣ ጠረንጴዛዎች እና ወንበሮች እንዲሁም ለሳኒተሪ እና ለቢውልዲንግ ኤሌክትሪካል ኢንስታሌሽን የተግባር ስልጠና መስጫ ወርክሾፖች አጠቃላይ የሌይአውት ስራ በማከናወን ከ6 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ስራ ሰርቷል፡፡ በዚህም የውድ ወርክ፣ የሜታል ማኑፋክቸሪንግ፣ የኤሌክትሪክ ኤሌክትሮኒክ እና የኮንስትራክሽን ዲፓርትመንቶች አሰልጣኞች የአንበሳውን ድርሻ ተወጥተዋል።
ከዚህ ባሻገር በዚሁ ሳምንት 41 ለሚሆኑ የኮሌጁ ሴት ሰልጣኞች የታብሌት ስጦታ ያበረከተውም ይህንኑ ቀን ታሳቢ በማድረግ መሆኑ አይዘነጋም፡፡
ምናልባት ማርች 8 የሴቶች ቀንን ስናከበር የወንዶችስ ቀን አይከበርም ወይ የሚል ጥያቄ ከተነሳ መልሱ ዓለም አቀፍ የወንዶች ቀን የሚከበረው ኖቬምበር (ኅዳር) 19 ሲሆን ከ1990ዎቹ ጀምሮ ከ80 በላይ በሚሆኑ ሀገራት ይከበራል ይሁን እንጂ እስከ አሁን በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዕውቅና አልተቸረውም፡፡
በመጨረሻም ለኮሌጃችን ሴት ሰራተኞች እና ሰልጣኞች ለማርች 8 እንኳን አደረሳችሁ እያልን መልካም የስኬት ጊዜ እንዲሆንላችሁ እንመኛለን፡፡
"በላቀ አግልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"