የታደሰው ካፌ በይፋ ስራ ጀመረ

Wingate News New Events in GWPTC

Posted by admin on |

Share: Facebook | Twitter | Whatsapp | Linkedin Visits: 74


የታደሰው ካፌ በይፋ ስራ ጀመረ

ረቡዕ:- መጋቢት 11 ቀን 2016 ዓ.ም

የታደሰው ካፌ በይፋ ስራ ጀመረ!!

ዕፁብ ድንቅ ሆኖ በመታደስመጋቢት 11 ቀን 2016 ዓ.ም ስራ የጀመረው የኮሌጁ ሰራተኞች መዝናኛ ክበብ ከምን ተነስቶ የት እንደደረሰ የሚያስቃኝ በወፍ በረር ለመዳሰስ ሞከረን፡፡

ኮሌጁ በዚህ ዓመት ከሰራቸው የብዙ ብዙ ስኬቶች አንዱ ነባሩን የሰራተኞች ካፌ ስርነቀላዊ እና እምርታዊ በሆነ ለውጥ ማደስ ነው፡፡ የዚህ ፕሮጀክት ዋና መሪ የዲራፍቲንግ ቴክኖሎጂ አሰልጣኝ እና የአርትቴክት ባለሙያ አሰልጣኝ ሳሙኤል ኤሊያስ ናቸው፡፡ ለዚህ ስራ ተነሳሽነታችሁን ያመጣው ገፊ ምክኒያት ምንድን ነው የሚለውን ጥያቄ ለአሰልጣኝ ሳሙኤል አነሳን፡፡ ‹‹በኮሌጁ የበላይ ኃላፊዎች ተቋማዊ ለውጥን ለማምጣት  በሚደረገው አዳዲስ ሀሳቦችን የማሰባሰብ ሂደት ላይ ተነስቼ በመጀመሪያ ደረጃ ለሰራተኞች ምቹ ከባቢ በመፍጠር ለሁሉም ሌሎች ተግባራት መነቃቃትን ይፈጥራል የሚል እምነት ስላደረብኝ እና ለዚህ ደግሞ ሰራተኛውን የመጠነ ዘመናዊ የሰራተኞች መዝናኛ ክበብ መኖሩ ግድ መሆኑን ስለተገነዘብኩ ይህንን እድሳት ለማድረግ አቅጄ ወደ ስራ ገባሁ፡፡›› ይላሉ አሰልጣኝ ሳሙኤል፡፡        

 

በዚህ ዕድሳት ላይ ስታንዳርዱን ያስጠበቁ ልዩ ልዩ አዳዲስ ተግባራት የተከናወኑ ሲሆን በአጠቃላይ 530 ካሬ ሜትር የሚሸፍን ስራ በጥራት እና በስፋት ተከናውኗል፡፡ ሁሉም ነገር በአዲስ መልኩ ነው የተሰራው፡፡ ለዚህ ስራ እውቀታቸውን የገለፁ፣ ክህሎታቸውን ያሳዩ፣ ልምዳቸውን ያጋራ ባለ አሻራዎች ብዙ መሆናቸውን ከአሰልጣኙ አንደበት ሰምተናል፡፡ ሰፊውን የሲቪል ስራ ኮንስትራክሽኖች፣ በሚያምር ውበት የኤሌክትሪክ ዝርጋታውን ኤሌክትሪክሲቲዎች፣ በሚስብ ዲዛይን የጥልፍ እና መጋረጃ ስራዎችን ጋርመንቶች፣ ማራኪ የእንጨት ስራዎችን ውድ ወርኮች፣ ውብ አደረጃጀቱን ሆቴሎች፣ ልዩ ልዩ የብረታብረት ምርቶችን ሜታል ወርኮች ወዘተ በመተባበር ሁሉም በባለቤትነት ስሜት አሻራቸውን እንዳስቀመጡ ታውቋል፡፡   

ይህ ስራ የእንጨት፣ የብረት ብረት፣ የኤሌክትሪክ ግባዓቶችን ጨምሮ አጠቃላይ ወጪ ወደ 13.5 ሚሊዮን ብር ኢንቨስት እንደተደረገበትም ከአሰልጣኝ ሳሙኤል መረጃ አግኝተናል፡፡ 


ለሰራተኞች ምቹ መዝናኛ ክበብን ከማደስ ባሻገር የስራው ሂደት ያመጣው ፋይዳ ይኖር ይሆን የሚል የመሰናበቻ ጥያቄ ለአርትቴክተሩ አነሳን፡፡ ‹‹በዚህ ስራ ላይ የተካፈሉ ብዙዎች እርስ በእርሳቸው በሙያቸው ልምድ ልውውጥ አድርገዋል፣ ከማሰልጠን ባሻገር ያለውን ሙያዊ ብቃት አሳይተዋል እንዲሁም ለሰልጣኞቻቸው የተግባር ልምምድ እንዲያደርጉ ዕድል ፈጥሮላቸዋል የሚል ሀሳብ ሰጥተውናል፡፡  

አሰልጣኝ ሳሙኤል ከዚህ ፕሮጀክት ውጪም ስማርት ክላስ መፍጠር የሚለውን ጽንሰ ሀሳብ ተጋርተው  ለሁሉም ዲፓርመንቶች የተገጠሙ ኢንተራክቲቭ ቦርዶች እውን እንዲሆኑ ትግበራው ላይ የአንበሳውን ድርሻ ወስደዋል፡፡


በዚህ ድንቅ ውበት ተከሽኖ ለአገልግሎት ዝግጁ የሆነውን መዝናኛ ክበብ በጥራት እና በተመጣጣኝ ዋጋ አገልግሎት እሰጣለሁ ብለው ጨረታውን ያሸነፉ ባለሀብት ዛሬ ስራቸውን  በይፋ የጀመሩ ሲሆን የዛሬውን የምሳ መስተንግዶ ለሁሉም ሰራተኞች በባለ ሀብቱ ሙሉ ወጪ በግብዣ መልኩ እንደሚሸፈን ታውቋል፡፡     


               "በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"

Leave a Comment: