ለሬጅስትራር ጽ/ቤት ባለሙያዎች ስልጠና ተሰጠ

Wingate News New Events in GWPTC

Posted by admin on | Last Updated by admin on

Share: Facebook | Twitter | Whatsapp | Linkedin Visits: 43


ለሬጅስትራር ጽ/ቤት ባለሙያዎች ስልጠና ተሰጠ

አርብ:- መጋቢት 13 ቀን 2016 ዓ.ም


ለሬጅስትራር ጽ/ቤት ባለሙያዎች ስልጠና ተሰጠ!!  


ለኮሌጁ ሬጅስትራር ጽ/ቤት ባለሙያዎች በደንበኛ አያያዝ ዙሪያ ዛሬ መጋቢት 13 ቀን 2016 ዓ.ም ስልጠና ተሰጠ፡፡ 

የደንበኞችን ፍላጎት መሰረት ያደረገ አገልግሎት ለመስጠት ታቅዶ ለጽ/ቤቱ ባለሙያዎች የተሰጠው ስልጠና በአገልግሎት አሰጣጡ ላይ ያሉ ፈታኝ ነገሮችን የሚያሳይ እና ማሻሻያ ስልቶችን የሚጠቁም ነው፡፡   

ስልጠናውን ያዘጋጀው በስልጠና እና አካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ዲን ቢሮ ስር የጥናት፣ ምርምርና ፐብሊኬሽን የስራ ክፍል ሲሆን ሬጅስትራር ጽ/ቤት ከሰልጣኝ ቅብላ እስከ ስልጠና ማጠናቀቂያ ሰርተፍኬት ስጦታ ድረስ  ባለው ጌዜ ከደንበኞች ጋር ሰፊ እና ቀጥተኛ ግንኙነት ስላለው ዘመኑ የደረሰበትን ቴክኖሎጂ በመጠቀም እና የደንበኞችን ፍላጎት ያማከለ አገልግሎት እንዲሰጥ ለማስቻል ታቅዶ መዘጋጀቱን ከስራ ክፍሉ አስተባባሪ ምስራቅ ደለሳ ማረጋገጥ ችለናል፡፡

አስተባባሪዋ አክለውም የጥናት፣ ምርምርና ፐብሊኬሽን የስራ ክፍል ተግባራዊ ጥናት እና ምርምር በማድረግ ክፍተቶች እንዲሞሉ ማድረግ ሲሆን ይህ ስልጠና እንዲሰጥ የተደረገውም በጥናቱ ግኝት መሰረት መስተካከል ካለባቸው ትግበራዎች አንዱ ስለሆነ ነው ብለዋል፡፡ ስልጠናው የተሰጠው ደግሞ በሄኖክ አብርሃም ነው፡፡ 


የኮሌጁ ደንበኞች የመጀመሪዎቹ ሰልጣኞች ናቸው፤ ሁለተኛዎቹም ሰልጣኞች ናቸው፤ ሶስተኛ እና አራተኛም እነሱ ስለሆነም በሁሉም የስራ እንቅስቃሴ ሰልጣኝ ተኮር ስራዎችን መስራት የሁል ጊዜ ተቀዳሚ ትኩረታችን ነው፡፡

               "በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"





Leave a Comment: