Posted by admin on |
Share: Facebook | Twitter | Whatsapp | Linkedin Visits: 45
ማክሰኞ:- መጋቢት 17 ቀን 2016 ዓ.ም
በኮንስትራክሽን ቴክኖሎጂ /ፊኒሽንግ/ እና ኢንፎርሜሽን ኮሚዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ /ICT/ ዲፓርትመንቶች መካከል በተደረገ የሰልጣኞች የእግር ኳስ ፍፃሜ ጨዋታ የኮንስትራክሽን ዘርፉ ሰልጣኞች ዋንጫውን አሸነፉ፡፡
ከየካቲት 6 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ከተለያዩ ዲፓርትመንቶች የተውጣጡ 14 ቡድኖች ሲጫወቱ ቆይተው ለፍፃሜ የደረሱት ሁለቱ ቡድኖች ዛሬ መጋቢት 17 ቀን 2016 ዓ.ም ከፍተኛ ፉክክር በታየበት አጓጊ ውድድር ተጫውተው ድል ለኮንስትራክሽን ሰልጣኞች ቀርባለች፡፡
ጨዋታው ምንም እንኳን 3 እኩል ሜዳ ላይ ቢጠናቀቅም መጨረሻ ላይ በተሰጠው የፍፁም ቅጣት ምት የኮንስትራክሽን /ፊኒሽንግ/ ዲፓርትመንት ግብ ጠባቂ አንድ ጎል በመከላከሉ በፍፁም ቅጣት ምቱ 5ለ4 በሆነ ትልቅ ትንቅንቅ ጨዋታው ተጠናቋል፡፡
በውድድሩ አሸናፊ ለሆኑት የዲፓርንመንቱ ሰልጣኞች የዋንጫ እና የገንዘብ ሸልማት የተበረከተላቸው ሲሆን ሽልማቱም በኮሌጁ ዋና ዲን በአቶ መለሰ ይግዛው አማካኝነት ተሰጥቷቸዋል፡፡
የእግር ኳስ ውድድሩ የተዘጋጀው በኮሌጁ ሰልጣኝ መማክርት አማካኝነት እንደሆነ እና ዓላማውም በሰልጣኞች መካከል የመተባበር እና የውድድር መንፈስን ለማሳደግ ታቅዶ እንደተዘጋጀ የመማክርቱ ም/ሰብሳቢ ሰልጣኝ ኤልያስ ሙልጌታ ነግሮናል፡፡
"በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"